ስለ እፎይታ ንብረት አስተዳደር ያወቅሁት…

ስለ እፎይታ ንብረት አስተዳደር …

ስለ እፎይታ ንብረት አስተዳደር ያወቅሁት አባቴ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶ ለቀብር አዲስ አበባ በመጣሁ ጊዜ ነው፡፡ አኔና አንድ ወንድሜ እና እህቴ ኖሮአችን በውጭ አገር በመሆኑ አባታችን ትቶት ያለፈውን በባንክ የሚገኝ ገንዘብ፤ የሚያከራያውን እና የምንኖርበትን የመኖሪያቤቶች፤ መኪና ወራሽነታችንን ለማረጋገጥ ከዚያም ለማስተዳደር እንዲሁም ከባንክ የሚገኘውን ገንዘብ አውጥተን ጥቅም ላይ ለማዋል ጊዜ ስላልነበረን ምን ማድረግ እንዳለብን በጣም ተጨንቀን በነበረበት ጊዜ ጓደኛዬን ስለሁኔታው ሳዋያት በሰጠችኝ ጥቆማ መሰረት የእፎይታ ካምፓኒ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ከሆኑት ከአቶ ፍቅሩ ጋር አስተዋወቀችኝ፡፡

ከዚያም ለአቶ ፍቅሩ ስለሁኔታው ሳስረዳቸው የርሳቸው ድርጅት handle ሊያደርገው እንደሚችል በገለጹልኝ መሰረት በዋጋ ተስማምተን ስራውን ከእናቴ ጋር በመሆን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው ቤተሰቡ ከነበረበት ጭንቀት የገላገሉን ከመሆኑም ሌላ ስለሚያከናውኑት ስራ ያላቸው እውቀት፤ በየቢሮው የሚያጋጥማቸውን ቢሮክራሲ እና ውጣውረድ በትግስት እና በዘዴ የማለፍ ችሎታቸው ፤ ሰው ለመርዳት ያላቸው ቀናነት እና ስራቸውን በታማኝነት ለመስራት የሚያሳዩትን ጥረት እናቴ ዘውትር በስልክ ትነግረኝ ስለነበር በጣም ደስተኛ ነበርኩ እንደ ቢዝነስ ሰው ሳይሆን እንደቤተሰብ በመሆን እናታችንን ከተጨማሪ ጭንቀት ስለገላገሏት በዚህ አጋጣሚበመላው ቤተሰቡ ስም ምስጋናዬ እንዲደርሳቸው እፈልጋለሁ፡፡

በአሁኑ ወቅትም ከቤተሰቡ ውክልና ወስደው አንደኛውን ቤት እያስተዳደሩልን ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም የአቶ ፍቅሩ ድርጅት ደንበኛ መሆን አውነትም እፎይታን የሚሰጥ በመሆኑ ተመሳሳይ ችግር ያለባችሁ ሰዎች ድርጅቱን በደንበኝነት ብትይዙ ከልባችሁ እፎይ እንደምትሉ ምስክርነቴን ስሰጥ በፍጹም እርግጠኛነት ነው፡፡

-የትናየት ሮም ፤ጣሊያን


Your Testimonials

Did we help you at some point in the past or even recently? Please leave us your comment and testimonials here

-Fikiru Tilahun, Efoyta’s General Manager.